የጸጥታ ተቋማት ባከናወኗቸው ተግባራት የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል

You are currently viewing የጸጥታ ተቋማት ባከናወኗቸው ተግባራት የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል

AMN ህዳር 13/2018

የጸጥታ ተቋማት ባከናወኗቸው ተግባራት የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ 807 ወንድ፣205 ሴት በድምሩ 1072 እጩ መኮንኖችን አስመርቋል።

በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛ አላማ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች በውጤታማነት ቀጥለዋል ያሉት ከንቲባዋ ይህንን ልማት ለማስቀጠል ሰላም እና ጸጥታ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ሰላም ለነገ የሚባል አለመሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ አዳነች የጸጥታ ተቋማት ባከናወኗቸው ተግባራት የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣን ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ እንደሚያስመሰግነውም ተናግረዋል።

ብቃት ያለው የሰው ሃይል በማፍራት በኩል ዉጤታማ ስራ መከናወኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች የአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ ወደ ኮሌጅ ማደጉ የደስታ ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳዳሩ ኮሌጁን በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ እንዲሆን የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ተመራቂ እጩ መኮንኖች ሀቀኛ የህዝብ አገልጋይ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review