መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ማረጋገጡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስታወቀ፡፡
20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የጋዜጠኞች ቡድን አባላት በሆሳዕና ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የስራ እንቅስቃሴ መጎብኘታቸው ተመላከተ፡፡

የአገልግሎቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ሻሜቦ እንደገለጹት በክልሉ ተገንብቶ ስራ የጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን፣ቀልጣፋ፣ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ አሰራርን መሰረት ያደረገ እና የህዝቡን ምሬት ያስቀረ ነውም ብለዋል።
በማዕከሉም 7 ተቋማት እና 20 የመንግስት አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑም ተነስቷል፡፡
ባለፉት ወራት በማዕከሉ 1ሺ 948 ተገልጋይ ተጠቃሚ ስለመሆናቸውም ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።
በተመስገን ይመር