ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት እና ከኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ አጄይ ባንጋ ጋር መወያየት ሁልጊዜም ቢሆን አስደሳች ነው” ብለዋል።
በመካሄድ ላይ ስላሉት በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ መወያየታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቁመዋል። ይኸውም በጤና፣ በኃይል ምንጭ እና የአየር ንብረት ጥበቃ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ጉዳይን የተመለከተ እንደነበር አመላክተዋል።