ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ውይይታችን በኢኮኖሚ እና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ አተኩረን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን የምናጠናክርባቸውን እድሎች አስመልክቶ የተካሄደ ነበር ብለዋል።
ብራዚል በቅርቡ የተካሄደው የCOP30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች እንዳሉም አመላክተዋል።
የአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራን የሚያራምድ በሚገባ የተሰናዳ መስተንግዶ እንዲኖረን ከልምዶች የተገኙ ሃሳቦችን መለዋወጡን አጠናክረን ለመቀጠል አቅደናል ሲሉም አክለዋል።