ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ውይይታችን የባለብዙ ወገን ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም እንደ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ ዘላቂ ልማት ያሉ የጋራ አለምአቀፋዊ ትኩረታችንን በምናጠናክርበት መንገድ ላይ ያጠነጠነ ነበር።
ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሊደረግ ስለሚችለው ድጋፍም መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡