ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሲንጋፖሩ አቻቸው ሎውረንስ ዎንግ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ማታ አዲስ አበባ ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋለሰ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ይህ ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት አጋርነትን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ ሲሆን፣ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር እድሎችን ለመዳሰስም ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል” ብለዋል።