ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን ይዘው ሲቀሳቀሱ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን ይዘው ሲቀሳቀሱ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN ህዳር 17/2018 ዓ.ም

ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን ይዘው ሲቀሳቀሱ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ።

ተጠርጣሪዎቹ በርዋ ከበደ፣ ሙላት አባይ፣ ሳሙኤል ሙሉጌታ እና ጃኮ ፔንዞ የተባሉ ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ልዩ ሆቴል አካባቢ ነው።

ሙላት አባይ የተባለው ተጠርጣሪ የተበደረውን ገንዘብ ልመልስልህ በማለት ሀሰተኛ መቶ ዶላር ለጓደኛው እንደሰጠው የገለፀው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግለሰቡም ከጓደኛው የተቀበለውን ዶላር ወደ ባንክ በመሄድ ለመመዘር ሲሞክር ሀሰተኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ ለፖሊስ ጥቆማ ሠጥቷል።

ፖሊስም ጥቆማውን መነሻ በማድረግ በወንጀሉ አንደኛውን ተጠርጣሪ ከነአባሪው በመያዝ በተደረገ የአካል ፍተሻም 1000 ሀሰተኛ ዩሮ ሊገኝበትም ችሏል።

ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ተግባር ሳሙኤል ሙሉጌታ የተባለው ተጠርጣሪ እንደሰጣቸው ለፖሊስ መረጃ በመስጠታቸው የተጠቀሰው ግለሰብ በቁጥጥር ስር በሚውልበት ጊዜም 1ሺህ400 ሀሰተኛ ዶላር እንደተገኘበትም የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

ምርመራው የማስፋት ስራውን ያላቆመው ፖሊስ ሶስተኛ ተጠርጣሪ ሀሰተኛ ዶላሩን ከየት እንዳመጣው ሲጠየቅ የውጭ ሀገር ዜጋ ወደሆነው አራተኛ ተጠርጣሪ ጃኮ ፔንዞ መምራቱን ያስታወሰው ፖሊስ መምሪያው የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው አራተኛው ተጠርጣሪም 5ሺህ 600 ሀሰተኛ ዶላር መገናኛ አካባቢ ይዞ ሲቀሳቀስ በቁጥጥር ስር የዋለና በአጠቃላይ ከ8ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ህብረተሰቡ ሐሰተኛ የውጭ ሀገርም ሆነ የሀገር ውስጥ የገንዘብ ኖቶችን ስርጭት ለመከላከል ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን መከላከል ይኖርበታል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አሳስቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review