በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል የተከሰተዉን የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እስካሁን ድረስ ምን ተከናወነ??
የመጀመሪያው የበሽታው ታማሚ ከተገኘበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በበሽታው ለተጠረጠሩ ለ73 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል
11 በሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተረጋግጧል
እነዚህ ታማሚዎች አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ቢሆንም የ6ቱ ህይወት አልፏል
የተቀሩት 5ቱ ደግሞ በህክምና ጣቢያ ወስጥ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ
የበሽታው ምልክቶች ከታየባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል
ከእነዚህም ውስጥ 119ኙ የክትትል ጊዜያቸውን ጨርሰው ከለይቶ ማቆያ እንዲወጡ ተደርጓል
ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተለያዩ ተቋማትን እና የሙያ ስብጥርን ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ተደራጅቷል
የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል
ማህበረሰብአቀፍ የቅኝት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ
ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ይገኛል
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የማከም ስራ እየተሰራ ነዉ
ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራዎች እየተሰሩ ነዉ
በብሔራዊ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (Incident Management System)ተቋቁሞ የፈጣን ምላሽ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ይገኛል።
የላቦራቶሪ የመመርመር አቅምን ከማሳደግ አኳያ የቫይረሱን ዘረ መል ለመለየት የሚያስችል የላቦራቶሪ አቅም ተገንብቷል
ተንቀሳቃሽ የላቦራቶሪ መመርመሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ግብአቶችን ወደክልሉ ተልከዋል
የተሰበሰቡት ሁሉም ናሙናዎች ረጅም ርቀት ሳይጓጓዙ ባሉበት ቦታ ለመመርመር ተችሏል
የበሽታውን መነሻ ለማወቅም አሁንም ጥረቶች እና ምርመራዎች እየተደረጉ ነዉ
ወረርሽኙ በተሰተባቸው አካባቢዎች የለይቶ ማከሚያ ማዕከላትን በማቋቋምና የሰለጠነ የሰውሃይል እና አስፈላጊውን የህከምና ግብአት በማደራጀት ለታማሚዎች የተጠናከረ የህክምና እርዳታ እየተሰጠ ይገኛል
ለታማሚዎችም የተሻለ ሕክምና ለመስጠት ከዚህ በፊት ወረርሽኙ ተከስቶባቸው ከነበሩ ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ ተደርጓል
የተገኘዉን ልምድ በመቅሰም ከዚህ በፊት ተሞክረው ጥሩ ውጤት ያስገኙ መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በመለየትና ወደሃገር ውስጥ በማስገባት ለታካሚዎች ተደራሽ እየሆኑ ይገኛሉ
በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ከነበራቸው የማህበረሰብ አካላት ጋር በበሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ Remsedevir የተባለ የፀረ ህዋስ መድሃኒት ወደ ሃገራችን ውስጥ ገብቷል
እስካሁን 16 ለሚሆኑ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ተብለው ለታሰቡ የህክምና ባለሙያዎች እና ታማሚዎች ለማድረስ ተችሏል
በሽታው ባልተገኘባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ወደፊት በሽታው ቢከሰት ሀከምና ለመስጠት የሚያስችሉ የለይቶ ማከሚያ እና ማቆያ ማዕከላት በሰለጠነ የሰው ሃይል፥ በግብዓትና በሌሎች ቁሳቁሶች እንዲሟሉ እየተደረገ ይገኛል
የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከሕብረተሰቡ ጋር ከሚደረገዉ የቅኝትና ልየታ ስራ በተጨማሪ በአገር በመውጫና መግቢያ ኬላዎች፥ በአየር ማረፊያዎች፥ እና ወረርሽኙ በተገኘባቸው አካባቢዎች የሚወጡና የሚገቡ ሰዎችን፣ ኬላዎችን በማቋቋም ሰፊ የልየታ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ
በሚቀጥሉት ሳምንታት ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ዘመቻ ጋርም በማስተሳሰር የቅኝትና የልየታ ተግባራት በሰፊው የሚከናወኑ ይሆናል።
ምንጭ – የጤና ሚኒስቴር