የደም መፍሰስ አለመቆም ችግር ምንድነው ?

You are currently viewing የደም መፍሰስ አለመቆም ችግር ምንድነው ?
  • Post category:ጤና

AMN- ህዳር 18/2018

ሰውነታችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲመታ፣ ሲጎዳ አንዳንዴ ደግሞ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የመድማት ችግር ሲመጣ የደም አለመርጋት ችግር ይባላል፡፡

በሰውነታችን ደም እንደ ፈለገ በደምስራችን ውስጥ እንዲዘዋወር እክል እዳይገጥመው የሚያደርግበት ስርዓት /ሄሞስታሰስ / የደም ስርዓተ ኡደት ነው፡፡

ይህ የደም ስረዓተ ኡደት ሲዛባ፣ ደም ባልተፈለጉ ቦታዎች ያለመርጋት ችግር ሊገጥመው ይችላል፡፡

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል የደም እና ተያያዥ ህመሞች ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶ/ር ኤፍሬም ሃይሌ ከ ኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የደም አለመርጋት ችግር ምንነት እና ምልክቶቹን አብራረተዋል፡፡

በዚህም በሰውነታችን ውስጥ ሶስት አይነት የደም ሴሎች አሉ ያሉት ዶር ኤፍሬም፣ እነዚህም ነጭ፣ ቀይ እና ፕላትሌትስ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ነጭ የደም ሴሎች ስራቸው በዋናነት በሽታ መከላከል መሆኑን እና ቀይ የደም ሴል ደግሞ ኦክስጅን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከሳንባ ወደ ሰውነት ወደ ልብ ማመላለስ ነው፡፡

ፕላትሌትስ የምንላቸው ደግሞ በቁጥራቸው በዛ ያሉ በመጠናቸው አነስ ያሉ ሲሆኑ፣ ስራቸው ደምን ማርጋት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህ ፕላትሌቶች የተቆረጠ የደም ስር ላይ በተርታ ሄደው በመደራራብ እንደወንፊት ይዘጉታል ብለዋል፡፡

ይህ መንገድ ሰውነታችን መድማትን የሚከላከልበት የመጀመሪያ ደረጃ እርምጃ ሲሆን፣ በዚህ አማካኝነት ደም ስሮችን ይዘጉታል ፣ በጉበት የሚመረቱ ከዘጠኝ በላይ የሚሆኑ ኳጉሌሽን ፋክተርስ የሚባል የደማው ቦታ ላይ እንደሚረባረቡ እና በዚህም ሰውነታችን በሁለት በሶስት ደቂቃ መድማት ያቆማል ብለዋል፡፡

ቮሉዩብራል ፋክተር፣ ፕላትሌት፣ ኳጉሌሽን ፋክተርስ የሚባሉት ሲጎሉ፣ የደም መድማት ችግር እንደሚከሰት ዶ/ር ኤፍሬም ሃይሌ ጠቅሰዋል፡፡

የደም አለመርጋት ምልክቶች

ሁለት አይነት የደም አለመርጋት ችግሮች እንዳሉ የገለፁት ዶ/ር ኤፍሬም፣ በተደጋጋሚ በነስር መቸገር፣ ሰገራ እና ሽንት ላይ ደም መቀላቀል፣ የድድ መድማት፣ በሴቶች የወር አበባ መጠኑ ሲበዛ ወይም የሚፈስበት ጊዜ እየረዘመ ሲያስቸግር የመጀመርያ አይነት የደም አለመርጋት ችግሮች ምልክቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የደም መርጋት ኡደት የሚቆጣጠሩ ቮሉዩብራል ፋክተር እና ፕላትሌት እጥረት በሰውነታችን ውስጥ ሲከሰት የደም አለመርጋት ችግር ይፈጠራል፡፡

ሁለተኛው የደም አለመርጋት ችግር ኳግሌሽን ፋክተርስ የሚባሉት በጉበት የሚመረቱት ፋክተሮች መጠናቸው በሰውነታችን ውስጥ ሲያንሱ ከበድ ያለ የደም መርጋት ችግር ያመጣሉ፡፡

ይህም ምንም አይነት የስኳርም ሆነ የግፊት ህመም ሳይኖር እድሜው ገና የሆነ ሰው ላይ በጭቅላት ውስጥ ድንገት የደም መድማት ያመጣሉ ብለዋል፡፡

በመገጣጠሚያ እና በአጥንት ውስጥ፣ ጡንቻ ውስጥ፣ በቀዶ ጥገና (ኦፕሬሽን) ጊዜ እና እናቶች በወሊድ ጊዜ ከባድ ደም መፍሰስ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

ይህም በጉበት ላይ የሚመረቱ የኳጉሌሽን ፋክተርሶች እጥረት ምክንያት የሚፈጠሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ህክምናው

ሁሉም የደም አለመርጋት አይነቶች ህክምና እንዳላቸው የገለጹት ዶ/ር ኤፍሬም፣ ማንኛውም ሰው እነዚህ አይነት ምልክቶች ሲገጠሙት ወደ ጤና ተቋም በመምጣት የደም አለመርጋት ችግሮችን መከላከል እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

በፍሬህይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review