የመከባበር እና የአብሮነት እሴት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍ በትኩረት ሊሠራ ይገባል

You are currently viewing የመከባበር እና የአብሮነት እሴት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍ በትኩረት ሊሠራ ይገባል

AMN- ህዳር 18/2018 ዓ.ም

የመቻቻል፣ የመካባበር እና የአብሮነት እሴት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍ የትምህርት ማህበረሰቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናገሩ::

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ዉድድር እና ያፓናል ዉይይት እያካሄደ ይገኛል::

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፣ በዓሉን በከተማዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ዝግጅቶች ሲያከብሩ መቆያታቸውን ገልጸዋል ::

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የሀገርን ስሜት በማጉላት በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ የምናከብረው በዓል እደሆነም ጠቅሰዋል ::

የመቻቻል፣ የመካባበርና የአብሮነት እሴት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍ የትምህርት ማህበረሰቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል ::

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሪት ፋይዛ መሀመድ በበኩላቸው፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በህዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነትን አሳድጓል ብለዋል ::

ቀኑ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መጎልበት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ የገለፁት ምክትል አፈ ጉባኤዋ፣ ለሀገር ልማት የድርሻዉን አጠናክሮ ቀጥሏልም ብለዋል ::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review