ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የሚካሄደውን 96ኛውን የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንድታዘጋጅ በሙሉ ድምፅ የተመረጠችው በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ ሲካሄድ በቆየው 93ኛ የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።
ከሦስት ወር በፊት ነሐሴ ላይ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ ተደርጎ በነበረው 26ኛው የኢንተርፖል አፍሪካ ሪጂናል ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ ቀጣዩን በ2027 የሚካሄደውን 27ኛውን የኢንተርፖል አፍሪካ ሪጅናል ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ መመረጧ እንደሚታወስ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል።