ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ብዝሀነት ወደ ልማት በመቀየር ለሀገር እድገት ሊሰሩ ይገባል

You are currently viewing ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ብዝሀነት ወደ ልማት በመቀየር ለሀገር እድገት ሊሰሩ ይገባል

AMN -ህዳር 19/2018 ዓ.ም

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ 20ኛውን የብሔር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በፓናል ውይይት እና በሌሎች መርሀ ግብሮች አክብሯል።

በመርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር)፣ የዘንድሮው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ኢትዮጵያ በማንሰራራት መንገድ ላይ ባለችበት ጊዜ የሚከበር መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

አንድነትን እና ህብረትን በማጠናከር የሀገሪቱን የልማት ግስጋሴ ማስቀጠል እንደሚገባም ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው ተናግረዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በአዲስ አበባ ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶሜ አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መግባባትን ለማረጋገጥ ብዙ እርቀት መጓዟን እና በዚህም ለውጥ ማስመዝገቧን ጠቁመው፣ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለምፍታትም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ በመስራት ላይ ትገኛለች ብለዋል።

የኢትዮጵያን ብዝሀነት ለመመልከት አዲስ አበባ አንዷ ማሳያ መሆኗን ያነሱት አቶሜ አበበ (ዶ/ር) እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ የሀገር አንድነትን በመጠበቅ ማረጋገጥ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።

በቤተልሔም አየነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review