የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ ነው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር ተናገሩ፡፡
ለዚህ ብሔራዊ ጥቅም ህዝቦች ከጫፍ እስከ ጫፍ በመነሳት በአንድነት የቆሙበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ አገኘው ተሻገር፣ ይህ ብሔራዊ ጥቅም በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲዊ መንገድ ሰጥቶ በመቀበል መርህ የሚፈፀም ነውም ብለዋል፡፡
የባህር በር ጥያቄ ከነውርነት ወጥቶ የመንግስት እና የህዝብ አጀንዳ ሆኖ ማየት የዘመኑ ትልቅ እምርታ መሆኑንም ነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር የ20ኛውን ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ከፋፋይ ነጠላ ትርክቶች ተወግደው ብሔራዊ ትርክት እንዲዳብር ባለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልፀዋል፡፡
በየዓመቱ ህዳር ወር ላይ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያ ቀን ነው ብለዋል፡፡
ሀብታሙ ሙለታ