የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የተጀመረውን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳካት የሚያስችል ነው

You are currently viewing የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የተጀመረውን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳካት የሚያስችል ነው
  • Post category:ኢኮኖሚ

AMN- ህዳር 19/2018 ዓ/ም

የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የተጀመረውን የኢኮኖሚ እድገት ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በከር ሻሌ ቆጠራው በሀገሪቱ የተጀመረውን የኢኮኖሚያ እድገት እንደሚያሳካ ጠቅሰው፤ ቆጠራው አነስተኛ፣ መካከለኛና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ያካትታል ብለዋል፡፡

ቆጠራው የሀገርን እድገትና የምርት ግመታን ለማካሄድ ከፍተኛ እገዛ ያለው በመሆኑ ለቆጠራው ዜጐች ትብብር እንዲያደርጉ አጽእኖት ስጥተው ተናግረዋል፡፡

መረጃው ለሀገር ፖሊሲ ግንባታ ሆኖ ስለሚያገለግል ለስኬቱ በየደረጃው ያሉ ሀላፊዎች እንዲሁም መረጃ ሰጪዎች ለመረጃ ስብሳቢዎች ትክክለኛ መረጃ በመስጠት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቆጠራው በ2019 ዓ/ም የኢትዮጵያ አጠቃላይ የምርት ቆጠራ ወይም ጂዲፒ ግመታ ላይ ክለሳ እንዲሁም የኢትዮጵያ ድህነት ምጣኔ ለመለካት መነሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአልማዝ ሙሉጌታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review