37ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል

You are currently viewing 37ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል

AMN -ሕዳር 19/ 2018 ዓ.ም.

37ኛውን የዓለም አቀፍ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴረሽን (ኢሠማኮ) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡

በመግለጫው ኮንፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ድርብሳ ለገሰ እንደገለጹት ከህዳር 23 እስከ 25 2018 ዓ/ም ከተለያዩ ሀገራት ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ የሰራተኞች ማህበራት ስብሰባዎች፣ የልምድ ልውውጦች፣ የስራ ጉብኝቶች እና የአለም አቀፉ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን(ITUC) ምክርቤት ስብሰባ እንደሚካሄድ ነው።

ኢሠማኮ በቀጣይ ቀናት የአፍሪካ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ቀንና የመላው ቻይና የሠራተኞች ማኅበራት የሥራ ጉብኝትን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሠራተኛ ማኅበራት ስብሰባዎችን እንደሚያካሔድ አስታውቋል።

ኢሠማኮ ከዓለም አቀፍ የሠራተኛ ማኅበራት ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት ተቀባይነት እና በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉት የልማት ሥራዎች ጉባኤው በአዲስ አበባ ከተማ እንዲካሄድ ምክንያት እንደሆነም ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለኤ ኤም ኤን ገልፀዋል።

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሠራተኛ ማኅበራት ተወካዮችን ጨምሮ ከ150 በላይ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ጉባኤው በማህበራቱ መካከል ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት ከማጠነከር ባለፈ ለሀገሪቱ ትልቅ የገፅታ ግንባታ ነው ሲል ኢሰማኮ በመግለጫው አስታውቋል።

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review