ፋይዳ የዲጂታል አሰራር ኢትዮጵያ 2025/30 በሁሉም ሰነዶች ላይ እንደ ቁልፍ መሠረት የተቀመጠ ነው

You are currently viewing ፋይዳ የዲጂታል አሰራር ኢትዮጵያ 2025/30 በሁሉም ሰነዶች ላይ እንደ ቁልፍ መሠረት የተቀመጠ ነው

AMN- ታኅሣሥ 14/2018 ዓ.ም

ፋይዳ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025/30 በሁሉም ሰነዶች ላይ እንደ ቁልፍ መሠረት የተቀመጠ መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ገለጹ።

ፋይዳ ዲጂታል ኢትዮጵያ አተገባበርን በተመለከተ ባደረጉት ገለጻ የፋይዳ መታወቅያ ትላልቅ ሰነዶች ላይ እንደ ቁልፍ ጉዳይ የተያያዘበትን ምክንያት አስረድተዋል።

በዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አካታችነትን እንደ ቁልፍ አድርጎ የያዘ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ህዝቡን በጋራ ወደ ኢኮኖሚ የምናመጣበት ትልቅ መሠረት ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

ፋይዳ መረጃን ሰብስቦ በቋት ውስጥ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ በሚሊየን የሚቆጠሩ መረጃዎችን የማረጋገጥ ፣ አገልግሎቶችን ለጠያቂ አካላት፣ ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማቅረብ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህን ሲያቀርብ በቀላሉ የይለፍ ቃል፣ በአሻራ፣ በገጽ መለያ በጣት አሻራ አድርጎ ከፍተኛ ደረጃ ባለው ዋስትና ዜጋው በአካል ሳይገኝ ከቤቱ ሆኖ የወረዳ፣ የክልል፣ የፌዴራል ተቋማትን አገልግሎቶችን በስልኩ እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል።

አገልግሎቱ ኔትዎርክ በሌለባቸው አከባቢዎችም እንዲሰራ ተደርጎ የተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ደንበኞች ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ አገልግሎት ይሄዱ እንደ ነበር ገልጸው፤ በአሁኑ የዳጂታል ኢትዮጵያ 2030 አሰራር ተልዕኮ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰው ተኮር አገልግሎታቸውን ለዜጋው በቅርበት ያቀርቡለታል ብለዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review