ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሼካ ዞን አማን ከተማ ለሚኖሩ የአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሚመራው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ስራ ከጀመረበት ጌዜ ጀምሮ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዛሬው እለት የተደረገው ድጋፍም ልጆቻቸው የአካል ጉዳት ገጥሟቸው ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ለተቸገሩ ወላጆችና ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለመማርም ሆነ ለመስራት ለተቸገሩ ወገኖቻች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡