AMN – ጥር 27 ፣ 2018 ዓ.ም
የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፣ ሀገራቸው ህጻናት ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያ አውዶችን እንዳይጠቀሙ እንደምታግድ አስታውቀዋል፡፡
ፔድሮ ሳንቼዝ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተካሄደ ጉባኤ ላይ እንገለጹት ፣ የማሕበራዊ ሚዲያ አውዶችን ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች እንዳይጠቀሙ ለማድረግ አቅዳለች፡፡
ዕገዳውን ተፈጻሚ ለማድረግ ፣ መንግሥት የማሕበራዊ አውድ ባለቤቶች የዕድሜ ማረጋገጫን ተግባራዊ እንድያደርጉ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ ነው ዘ ስታር የዘገበው፡፡
“ማህበራዊ ሚዲያ ሕግ የሚጣስባቸው ፣ ወንጀሎች ቸል የሚባሉባቸው እና ከእውነት ይልቅ ስሁት መረጃዎች ዋጋ የሚያገኙባቸው ሆነዋል ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተችተዋል፡፡
የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በጥላቻ ጥቃት ተጎጂዎች መሆናቸውን ነው ፔድሮ ሳንቼዝ የተጠቀሱት፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ዙሪያ ሐገራት ማሕበራዊ ሚዲያን በዕድሜ የመገደብና ለህጻናት ተደራሽ እንዳይኑ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
ባለፈው ወር በወጣ መረጃ መሠረት ፣ 5 ሚሊየን አካውንቶች እንዲዘጉ ያደረገ እገዳን አውስትራሊያ ተግባራዊ አድርጋለች፡፡ የፈረንሳይ ሕግ አውጪዎችም ከ15 ዓመት በታች ሕጻናት እንደ ‘ፌስቡክ’ ፣ ‘ኢንስታግራም’ ፣ ‘ቲክቶክ’ እና ‘ስናፕቻት’ ያሉ መተግበሪያዎችን እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ አጽድቀዋል፡፡
የስፔን ሕግ ፣ በ‘ቲክቶክ’ ፣ ‘ኢንስታግራም’ እና ‘ግሮክ’ በመሳሰሉት አውዶች ላይ ለሚፈጸሙ ጥሰቶች የተቋማቱን ሥራ አስፈጻሚዎችን ተጠያቂ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ጠቅሰዋል፡፡
ከእንግዲህ ከኮድ ጀርባ መደበቅ አብቅቷል ፣ ቴክኖሎጂ ገለልተኛ ነው የሚባል ነገርም አክትሟል ሲሉ ጠንከር ያሉ ድንጋጌዎችን ለማሳለፍ ሌሎች የአውሮፓ ሐገራትም ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ታደሰ ሽፈራው