በአዲስ አበባ እየተሰጠ ያለው የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ለሁለት ቀናት ተራዘመ

You are currently viewing በአዲስ አበባ እየተሰጠ ያለው የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ለሁለት ቀናት ተራዘመ

AMN – ጥቅምት 01/2017 ዓ.ም

በከተማው በዘመቻ እየተሰጠ ያለውን የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ለተጨማሪ ሁለት ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክትባት ዘመቻው በአዲስ አበባ ከመስከረም 27 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት እየተሰጠ ቆይቷል።

ሆኖም በከተማ አስተዳደሩ ክትባቱን ማግኘት ያለባቸው ሁሉንም ህጻናት ለማዳረስ በማለም ለሁለት ቀናት በማራዘም ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2017 ዓ.ም ክትባቱ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በዚህም ወላጆች እና አሳዳጊዎች እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን በእነዚህ ቀናት በማስከተብ ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ጥሪ አቅርቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review