የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብሔራዊ ደረጃ መከበር ሀገርን ከነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ለተደረገዉ ተጋድሎ አዉቅናን መስጠት ነዉ- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሀመድ

You are currently viewing የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብሔራዊ ደረጃ መከበር ሀገርን ከነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ለተደረገዉ ተጋድሎ አዉቅናን መስጠት ነዉ- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሀመድ

AMN – ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብሔራዊ ደረጃ መከበር ዓላማ መሰረታዊ የሰንደቅ ዓላማን ቀን በተገቢዉ መንገድ ከማስረጽ ባሻገር፤ ሀገርን ከነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ለተደረገዉ ተጋድሎ አዉቅናን መስጠት ነዉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ፋይዛ መሀመድ ገለጹ።

17ኛዉ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ተከብሯል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ፋይዛ መሀመድን ጨምሮ የምክርቤት አባላት እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።

ምክትል አፈ ጉባኤ ፋይዛ መሀመድ፤ የቀኑ በብሔራዊ ደረጃ መከበር ዓላማዉ መሰረታዊ የሰንደቅ ዓላማን በተገቢዉ መንገድ ከማስረጽ ባሻገር ሀገርን ከነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ለተደረገዉ ተጋድሎ አዉቅናን መስጠት ነዉ ብለዋል።

ጀግኖች አባቶች ተዋድቀዉ ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ እንዳደረጉት የገለጹት ምክትል አፈጉባኤዋ፤ኢትዮጵያ የጀመረችዉን ታላቅ የልማትና የብልጽግና ጉዞ ከዳር በማድረስ ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ እናድርግ ሲሉም አክለዋል፡፡

በአለማየሁ አዲሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review