በምሥራቃዊ ቱርኪዬ ርዕደ መሬት መከሰቱ ተሰማ

You are currently viewing በምሥራቃዊ ቱርኪዬ ርዕደ መሬት መከሰቱ ተሰማ

AMN – ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም

በምሥራቃዊ ቱርኪዬ ማላቲያ ግዛት በሬክተር ስኬል 5.9 የሆነ ርዕደ መሬት መከሰቱን የሀገሪቱ ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባለሥልጣኑ አያይዞም አደጋውን ተከትሎ የተከሰተ ውድመት ስለመኖሩ የደረሰው መረጃ እንደሌለ ገልጿል።

ርዕደ መሬቱ በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 4:46 አካባቢ በሀገሪቱ በስተምሥራቅ ከምትገኘው ማላያ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ካሌ በተሰኘ አካባቢ መከሰቱንም አመላክቷል።

የተቋሙ ሠራተኞችም ለማንኛውም ሊፈጠር ለሚችል አደጋ ፈጥኖ ለመድረስ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ ነው የገለጸው።

የርዕደ መሬቱ ንዝረት እስከ ሶሪያ ሃሳካህ ዴር አል ዞር እና አሌፖ ግዛቶች ድረስ መሰማቱን የሀገሪቱን መንግሥት መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል።

የአውሮፓ ሜዲትራኒያን የሥነ-ምድር ጥናት ማዕከል እንደገለጸው ርዕደ መሬቱ በሬክተር ስኬል 6.1 የተለካ እና ከመሬት ሥር 9 ኪሎሜትር ጥልቀት ላይ የተከሰተ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review