ሀገራት የእዳ መክፈል አቅማቸው እየታየ የእፎይታ ጊዜ ሊያገኙ ይገባል:- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

You are currently viewing ሀገራት የእዳ መክፈል አቅማቸው እየታየ የእፎይታ ጊዜ ሊያገኙ ይገባል:- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

AMN – ጥቅምት 15/ 2017 ዓ.ም

ሀገራት የእዳ መክፈል አቅማቸው እየታየ የእፎይታ ጊዜ ሊያገኙ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና በዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል፡፡

ልዑኩ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ አመራሮች እንዲሁም የቡድን-20 የወቅቱ ሊቀመንበር የሆነችው ብራዚል በመሩት የግሎባል ሉዓላዊ የዕዳ ድርድር ጉባኤ ላይ ተሳትፏል፡፡

በጉባኤው ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ አጋርተዋል፡፡

ሀገራት እዳቸውን ለመክፈል የሚያደርጉት በጎ ጥረቶች እየታዩ በፍጥነት ጊዜያዊ የእዳ ክፍያ እፎይታ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ፕሮግራሞች በቦርዱ መጽደቅን ተከትሎ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ የእዳ ማሸጋሸግ ሂደቱ የሚጠናቀቅበት አሰራር የማስፈን አዲስ ሃሳብም አቅርበዋል።

የስብሰባው ተሳታፊዎችም የእዳ ሽግሽግ ሂደት ውጤታማነት፣ ተገማችነት እና የጊዜ ሰሌዳ አስፈላጊነት ላይ መስማማታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review