AMN- ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላንን ጥቅምት 26 እንደሚረከብ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክሰኞ እለት የሚረከበው A350- 1000 አውሮፕላን ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑን አየር መንገዱ መግለጹ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን A350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላን ”Ethiopia land of origins” በሚል ነው የሰየመው።
A350-1000 አውሮፕላን 400 መቀመጫዎች ያሉት ነው።
አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየሰራ ነው።
በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል።
አየር መንገዱ የሚረከበው A350-1000 አውሮፕላንም በአይነቱ ልዩና በአፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑ መገለጹ እንደሚታወስ ኢዜአ ዘግቧል፡፡