የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

AMN-ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው።

የምክር ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር እና የቋሚ ኮሚቴው አባላት የቢሮውን የስራ እንቅስቃሴ በአካል እየገመገሙ ይገኛሉ።

በመርሐ-ግብሩም የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)ን ጨምሮ የየዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።

የቢሮው ኃላፊ የሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸምን አስመልክተው እንደተናገሩት፤ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ የቢሮውን ስራዎች ውስንነትና ጥንካሬ በየጊዜው አየተከታተለ መገምገሙና አቅጣጫ መስጠቱ ለቢሮው ጥንካሬ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የ2017 የትምህርት ዘመን በተቀመጠለት ካላንደር መሠረት መጀመሩንና ሂደቱም መገምገሙን ተናግረዋል።

ቢሮው በኮሪደር ልማት ምክንያት ከፒያሳ እና ከ4 ኪሎ አካባቢ የተነሱ ተማሪዎችን በትክክል በመመዝገብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ትምህርት ቤት እንዲያገኙ መደረጉንና በዚህም ስኬታማ ስራ መሠራቱን ዶክተር ዘላለም አስረድተዋል።

በምትኩ ተሸመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review