በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ለማሸነፍ ተቃርበዋል

AMN – ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የፉክክሩን አሸናፊ የሚበይኑት ሰባት ግዛቶች መካከል ሰሜን ካሮላይና እና ጆርጂያ ላይ ዶናልድ ትራምፕ አሸንፈዋል።

በቀጣይ አሪዞና፣ ኔቫዳ፣ ሚሺጋን፣ ፔንሲልቫኒያ እና ዊስከንሰን የምርጫው የፉክክር ማዕከል ናቸው።

የምርጫው ፉክክር ዋንኛ ትኩረት የሆኑት በእነዚህ ሰባት ግዛቶች እስካሁን ባለው ሁኔታ ዶናልድ ትራምፕ በተቀሩት አምስቱም ግዛቶች እየመሩ ነው።

በተለይ 19 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ባለው ፔንሰልቨኒያ ላይ ዶናልድ ትራምፕ የሚያሸነፉ ከሆነ ምርጫው ለማሸነፍ ወደሚረዳቸው 270 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ለማግኘት ይቃረባሉ።

ትራምፕ በፔንሲልቨኒያ ግዛት ላይ የሚያሸንፉ ከሆነ ከወሳኞቹ ግዛቶች አንድ ተጨማሪ ግዛት ብቻ ነው ማሸነፍ የሚጠበቅባቸው።

እንድ ቢቢሲ ዘገባ ይህ ከሆነ ደግሞ የዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት የሚደመደም ይሆናል።

በአሳየናቸው ክፍሌ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review