AMN- ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም
የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጁሊዬስ ማዳ ቢዮ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው “ከረሃብ ነጻ ዓለም” ጉባኤ ላይ እንደሚካፈሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።