ኢትዮጵያ የአየር ሁኔታን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማጋራት የሚያስችላትን ፕርጀክት ይፋ አደረገች

You are currently viewing ኢትዮጵያ የአየር ሁኔታን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማጋራት የሚያስችላትን ፕርጀክት ይፋ አደረገች

AMN- ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የአየር ሁኔታ መከታተያ ጣቢያ በማቋቋምና መረጃ በመሰብሰብ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማጋራት የሚያስችላትን ፕርጀክት ይፋ አድርጋለች።

“ዓለም አቀፍ መሰረታዊ ምልከታ አውታር” የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት ከአየር ትንበያ መረጃ ጋር በተያያዘ ያለውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላት ያለመ ስለመሆኑ ተነግሯል።

በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ እንደተነገረው 9 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጀው ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በመንግስታቱ ድርጅት ባለብዙ አጋር ፈንድ እንደሚሸፈን ተነግሯል።

በአዲስ አበባ፣ በነገሌ ቦረና፣ በጅግጅጋና በጋምቤላ በሚተገበረዉ በዚህ ፕሮጀክት ያሉ የገፀ ምድርና የከፍታ የአየር ትንበያ ጣቢያዎችን ወደ አውቶማቲክ የመቀየር ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ተጨማሪ የአየር ትንበያ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች እንደሚቋቋሙም በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል።

መረጃን ያለማቋረጥ በመሰብሰብ እንዲሁም ከተቀረው ዓለም መረጃ በመቀበልና በመተንተን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የሚያግዘው ይህ ፕሮጀክት ለ3 ዓመታትን ይፈጃል ተብሏል።

በትዕግስት መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review