ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ላይ ያላት ድርሻ እንዲጨምር የቱሪዝም ልማት ፖሊሲዋን ማሻሻል ይገባታል፡-የቱሪዝም ሚኒስቴር

AMN – ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ላይ ያላት ድርሻ እንዲጨምር የቱሪዝም ልማት ፖሊሲዋን ማሻሻል እንደሚገባት የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የክልልና ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ተወካዮች በኢትዮጵያ የቱሪዝም ፓሊሲ ክለሳ ዙሪያ ምክክር እያደረጉ ነው።

በምክክሩ በዓለማችን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የቱሪዝም ዘርፍ በ3 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱ ተነግሯል።

አጠቃላይ ለአገራዊ የምርት ዕድገት 10 በመቶ ድርሻ ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ከቴክኖሎጂ ዕድገት እና ከሰዎች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ለስራ ዕድል ፈጠራና ለአገራዊ ዕድገት ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያም ከዚህ ዘርፍ ተጠቃሚ እንድትሆን ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቱሪዝም ልማት ፖሊሲዋን ማሻሻል እንደሚገባት በምክክሩ ላይ ተነስቷል።

ይህ ፖሊሲ ለኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ለባህላዊ ዕድገት አስተዋፅኦ ያደረገ ቢሆንም ዓለም አቀፍ የገበያ ተወዳዳሪነትን በማረጋገጥ፣ነባርና አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት እንዲሁም አገራዊ ተጠቃሚነትን በሚፈለገው ደረጃ በማምጣት ረገድ ውስንነቶች እንደነበሩት ተጠቅሷል።

ፓሊሲው ሲከለስ የቱሪዝም ቴክኖሎጂን ከፈጠራ ጋር ማቀናጀት እና አገሪቱ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ያላት ድርሻ ማሻሻል ላይ እንደሚያተኩር ተነግሯል።

በትዕግስት መንግሥቱ

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review