የአፍሪካ ሀገራት የስርዓተ- ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ውይይት ተጠናቀቀ

You are currently viewing የአፍሪካ ሀገራት የስርዓተ- ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ውይይት ተጠናቀቀ

AMN – ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ሀገራት የስርዓተ- ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ውይይት የተለያዩ ውሣኔዎችን በማፅደቅ ተጠናቋል።

የአፍሪካ ሀገራት የስርዓተ- ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ስብሰባ ከቀረቡት ጉዳዮች ዋነኛው በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በተመለከተ በሴቶች እና ታዳጊ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም የአፍሪካ ህብረት ስምምነት ነው።

ጉዳዩ ወቅታዊ እና ታሪካዊ እንደሆነና ለተጠቂዎች ፍትህ ተደራሽ ለማድረግ ፣ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ለማስፈን የሚያስችል፣ ተጨባጭ ሁሉን አቀፍ ምላሽ ለመስጠት የአፍሪካ ዝግጁነትን ማሳወቅ እንደሆነ ተገልጿል።

ስምምነቱ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ ለመሪዎች ስብሰባ ከመቅረቡ በፊት በአፍሪካ ህብረት አስራር መሰረት የህግና ፖሊሲ ክፍል እንዲመለከተው በመስማማት ፀድቋል።

ኢትዮጲያን ጨምሮ ሪፖርት ላቀረቡ አባል ሀገራት አድናቆት በመስጠት ሌሎች ያላቀረቡ ሀገሮች እንዲያቀርቡ ጥሪ በማስተላለፍ እንደ አህጉር የተዘጋጀው ሪፖርትም ይፀድቃል ተብሏል።

በሁለት ቀን ቆይታ ውይይት የተካሄደባቸውን የጸደቁ የዝርዝር ጉዳዮች ቃለ ጉባዔ እና ግብዓት የተሰጠባቸው የአፍሪካ ቤጂንግ -30 ሪፖርት እንዲሁም ለሚቀጥለው ዓለም አቀፍ የ(ሲ ኤስ ደብሊው) ስብሰባ የሚቀርበው የአፍሪካ የጋራ አቋምን በማፀደቅ በስኬት መጠናቀቁን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትየጲያም የCSW ቢሮ አባል ሆና እንደመመረጧ ይህ አህጉራዊ አቋም በማስተዋወቅና በአባል ሀገራት ወደ ተግባር እንዲገባ የድርሻዋን በሚገባ እንደምትወጣ በመድረኩ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review