የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ያወጣቸውን ሁለት የሰሊጥ ዝርያዎች ለአርሶ አደሩ ለማዳረስ እየሰራ ነው

AMN – ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ያወጣቸውን ሁለት የሰሊጥ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ለማዳረስ የዘር ብዜት ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ማዕከላትና ፋሲሊቲዎች ማኔጅመንት ዳይሬክተር ኢብሳ አልይ እንደገለጹት የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ያገኛቸውን የሰሊጥ ዝርያዎችን ምርጥ ዘር በማዛባት ለአርሶ አደሩ እያዳረሰ ቆይቷል።

ዩኒቨርሲቲው በምርምር ያገኛቸውን የሰብል፣ የእንስሳትና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማላመድ፣ የማስፋፋትና የማዳረስ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

ምርጥ ዘሮች የማባዛት ስራው በዩኒቨርሲቲው የምርምር ማዕከላት፣ በገበሬዎች ማሰልጠኛ ጣቢያ እና በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ እንደሚያከናውንም ጠቅሰዋል።

የሰሊጥ ዝርያዎቹ ድርቅን ተቋቁመው በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በሄክታር ከ7 እስከ 8 ኩንታል ምርት የሚሰጡ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በምርምር የወጡት ሁለቱ የሰሊጥ ዝርያዎች “በሃ ነጮ እና በሃ ዘይት” የሚሰኙ ሲሆን፤ በብሔራዊ ደረጃ ምርታማነታቸው ተረጋግጦ የተለቀቁ ናቸው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review