ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በሶቺ ፍሪያማ ውይይት አካሂደዋል።

ሁሉቱ ሚኒስትሮች የጋራ ጥቅምን መሠረት ባደረጉ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ሁለቱ አካላት የሁለቱን አገራት ግንኙነት በተለይም የኢኮኖሚ ዘርፍ የበለጠ ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

የጋራ ውይይቱ የተካሄደው ዛሬ ከሚጀመረው የመጀመሪያው የአፍሪካ ሩስያ ሚኒስትሮች ትብብር ፎረም የጋር ስብሰባ አስቀድሞ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review