
AMN- ህዳር 5/2017 ዓ.ም
የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፣የመካከለኛው ምሥራቅ ኤዥያና ፓሲፊክ አገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ንጉሥ ከበደ እና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
የጂያንሱ ግዛት ገዥ እና የግዛቷ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና መልሕቅ ኩባንያዎች አመራሮች በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የልዑካን ቡድኑ ዛሬ በአዲስ አበባ በሚከፈተው የቻይና-አፍሪካ(ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ ላይም ይሳተፋል።
ጂያንሱ የቻይናዋ ሁለተኛዋ ግዙፍ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ግዛት ስትሆን 76 ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሚያወጡ የኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው እንደሚገኙ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።