ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስን መልሶ ለማልማት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል- አቶ ኦርዲን በድሪ

You are currently viewing ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስን መልሶ ለማልማት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል- አቶ ኦርዲን በድሪ

AMN- ህዳር 5/2017 ዓ.ም

ማህበረሰቡን በማሳተፍ ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስን መልሶ ለማልማት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የሐረሪ ክልል ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ መልሶ ማልማት ላደረገው የልማት ተሳትፎ የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

በሐረሪ ክልል ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ህልውና አስጠብቆ በኢኮኖሚ አልቆ ለማቆየት የመልሶ ማልማት ስራ መከናወኑ ይታወሳል።

የክልሉ መንግስት ማህበረሰቡን ብሎም ተቋማትን በማሳተፍ መልሶ ለማልማት ባደረገው እንቅስቃሴ በራስ ተነሳሽነት በጀጎል ውስጥ የሚገኙ መንገዶችን በማልማት እና በማስዋብ ውጤታማ ስራ መከናወኑ ተመላክቷል።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ እንደገለፁት፤ ማህበረሰቡን በማሳተፍ ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስን መልሶ ለማልማት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

ቅርሱ ሰዎች የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን የሚመሩበት ህያው በመሆኑ ቋሚ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል።

መንግስት ከቅርስ ጥበቃው በተጨመሪ ባህልና ወጉን ጠብቆ ለማቆየት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በመጠቆም ተቋማት እና ህብረተሰቡ በቅርስ ጥበቃ ስራው ላይ ላደረጉት ተሳተፎ አመስግነዋል።

በቀጣይም ተቋማት እና ማህበረሰቡ የጀመሩትን የልማት ተሳትፎ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሐረሪ ክልል ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ነቢል ዩሱፍ በበኩላቸው ምክር ቤቱ በቀጣይም በክልሉ የሚከነወኑ የመሰረተ ልማቶችን በመደገፍ የበኩሉን አሻራ እንደሚያኖር አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review