የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ይዘቱንና ፋይዳውን ከፍ አድርጎ ለማክበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው-የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት

AMN-ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ይዘቱንና ፋይዳውን ከፍ አድርጎ ለማክበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ ሮ ፀሀይ ወራሳ በዓሉን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ወቅቱን ባገናዘበ ፣ ይዘቱንና ፋይዳውን ከፍ አድርጎ ኅብረብሄራዊ አንድነትንና ትስስርን ባጎላ መልኩ ለማክበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል::

ያለፉት በዓላት በርካታ ማሕበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች የተገኙበት እንደነበር ያስታወሱት አፈጉባኤዋ በዋናነት የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና አብሮነት የተጠናከረበት እንዲሁም ብዝሃ ባህሎችና እሴቶች እንዲለዋወጡ ምቹ አጋጣሚ የተፈጠረበት እንደነበር መናገራቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review