75ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል ፡- የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

You are currently viewing 75ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል ፡- የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

AMN- ህዳር 11/2017 ዓ.ም

75ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ በማቋቋም ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ተግባር ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።

320 የሚደርሱት የቀድሞው ተዋጊዎች በነገው እለት የትጥቅ ርክክብ እንደሚደረጉም ተመላክቷል።

የፕሪቶሪያ ስምምነቱን ተከትሎ የቀድሞ ተዋጊዎችን የማቋቋም ተግባር እንዲያከናውን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ህዳር 3/ 2015 መቋቋሙ ይታወቃል ።

ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋምና ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል ሃብት ከማሰባሰብ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን ተናግረዋል።

ለዚህም ማስፈጸሚያ የሃብት የማሰባሰብ ተግባር ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል ኮሚሽነሩ።

በቅድመ ዝግጅት ምእራፍ ስራው ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርና ከሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ጋር በመሆን የተሃድሶ ፕሮግራምና ተሳታፊዎችን የመለየት ተግባር ተከናውኗል ብለዋል ኮሚሽነር ተመስገን ።

ከ 7 ክልሎች የተውጣጡ ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞውን ተዋጊዎችንም ለማቋቋም ከ760 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡

በ2 አመታት ጊዜ ውስጥ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋምና ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል ተግባር ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እንደሚቀጥል በጋዜጣዊ መግለጫው ተመላክቷል፡፡

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review