እንደ ሕዝብ የምናልመውን መልካም ተስፋ በተግባራዊ ሥራ መደገፍ ይገባል-ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

You are currently viewing እንደ ሕዝብ የምናልመውን መልካም ተስፋ በተግባራዊ ሥራ መደገፍ ይገባል-ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

AMN- ኅዳር 11/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ ለፌደራል ተቋማት የመንግሥት ሠራተኞች በተዘጋጀ መነሻ ጽሑፍ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ እንደ ሕዝብ የምናልመውን መልካም ተስፋ በተግባራዊ ሥራ መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኛ ለአገር ተጨማሪ ዕድገት የሚያመጡ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ለማከናወን የላቀ ሞያዊ ብቃት በመላበስ ለተግባራዊነታቸው በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፣ ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን በመሆኗ በመንግሥት በኩል ለአገር ዕድገት የተቀመጡ የለውጥ ሕልሞች በዲፕሎማሲው ዘርፍ እውን ይሆኑ ዘንድ በትጋት እና በሕብረብሔራዊነት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

በአገሪቱ እየተደረጉ ያሉ የለውጥ ሥራዎችን በተገቢው በመረዳት እና ከከፋፋይ ትርክት በመውጣት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት መጣር እንደሚገባ አንስተዋል።

የውይይት መነሻ ጽሑፉን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ አቅርበዋል።

በጽሑፋቸው እንደ አገር ባለፉት አምስት ዓመታት በሁለንተናዊ ዘርፎች የተደረጉ ለውጦች እና ያስገኟቸውን ውጤቶች አብራርተዋል።

በቀረበው መነሻ ጽሑፍ ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄ እና አስተያዬት ቀርቦ ከመድረክ በተሰጠ ምላሽ እና ማብራሪያ ውይይቱ መጠናቀቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review