በሰሜን ጎንደር ዞን የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሰላም ጥሪውን በመቀበል ለሠራዊቱ እጅ እየሰጡ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing በሰሜን ጎንደር ዞን የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሰላም ጥሪውን በመቀበል ለሠራዊቱ እጅ እየሰጡ መሆኑ ተገለፀ
  • Post category:ወክታዊ

AMN ህዳር 16/2017 ዓ .ም

መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል የፅንፈኛው ቡድን በሰሜን ጎንደር ዞን ለመከላከያ ሠራዊት በሰላማዊ መንገድ እጅ እየሰጠ እንደሚገኝ የሰሜን ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖሰት ሰብሳቢ ሜጀር ጄኔራል አማረ ገብሩ ገልፀዋል።

ሠራዊቱ በርካታ ሀገራዊ ተልዕኮዎች የሚጠብቁት እንደመሆኑ መጠን ከፅንፈኛ ቡድኑ ነፃ የወጡ ቀጠናዎችን በራሱ የፀጥታ መዋቅር ዘላቂ ሰላማቸው እንዲረጋገጡ በስልጠና የማብቃት እና ዘላቂነት ያለው ድጋፍ መስጠት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ህዝቡን በመዝረፍና ሰላም በማሳጣት ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን የተናገሩት እጅ የሰጡት የቡድኑ አባላት አሁን የተሰጣቸውን የሰላም ምህረት በመጠቀም የበደሉትን ህዝብ ለመካስ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው በሰላም ማስከበር እና የተሃድሶ ሰልጠና ወስደው ከፀጥታ አካላት ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የቀረበላቸውን የሰላም ጥያቄ ተቀብለው እጅ የሰጡ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች አስፈላጊውን ሁሉ እንክብካቤ በሠራዊቱ እየተደረገላቸው እንዳለም ከመከላከያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

All reactions:

221221

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review