የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሻለ ሁኔታ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ህዳር 17/2017 ዓ .ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፈት መልእክት የዘንድሮውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሻለ ሁኔታ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በዚሁ መሰረት ዛሬ ከሆቴል ባለቤቶች እና ከዘርፉ አካላት ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በውይይቱ እንደተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትንና እንግዳ ተቀባይነታችንን አጉልተን በማሳየት በላቀ አገልግሎት ሰጪነት እንድናስተናግድ እንዲሁም ከተማችንን የቱሪዝምና የኮንፍራንስ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስራ ይበልጥ በሚያጠናክር አግባብ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ትላልቅ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉባኤዎች ወደ ከተማችን እንዲመጡ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ተግባብተናልም ሲሉ ነው ከንቲባዋ መልእክታቸውን ያስተላለፉት ።

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review