በመዲናዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት የተከናወኑ ተግባራት እና በአምራች፣ በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ያለዉ የግብይት ሠንሠለት አፈጻጸም የተሻለ ነው፦አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN-ኅዳር -21/201 7ዓ.ም

በመዲናዋ አዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በገበያ ማእከላት፣በእሁድና በቅዳሜ ገበያ፣በመጋዘን ክምችት፣ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ያለዉ የግብይት ስርዓት እንዲሁም በአምራች በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ያለዉ የግብይት ሠንሠለት አፈፃፀሙ የተሻለ መሆኑን ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ህገ ወጥነትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የተቋቋመዉ የገበያ ማረጋጋት እና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሀይል ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ሴክተር ተቋማትና አመራሮች ጋር እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ ።

ግብረ ኃይሉም በመሠረታዊነት በምርት አቅርቦትና ስርጭት ፣ የገቢ ምንጭ ማስፋትና ገቢ መሰብሰብ፣ የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የህግ ማስከበር ስርዓት እንዲሁም የመረጃ ተደራሽነት ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል ።

በግምገማዊ ዉይይቱም ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ከቀረበዉ ሪፖርትና ከቀረበዉ አስተያየት በመነሳት እንደተናገሩት ግብረሁይሉ የተደራጀዉ ችግሮችን እንዲፈተና አቅጣጫ እያስቀመጠ እንዲመራ መሆኑን ጠቁመዉ በዚህ ረገድ ተስፋ ሰጪ ዉጤቶች ማስመዝገብ ቢቻልም ስራዉ የአመራሩን ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ይበልጥ በየደረጃዉ ስራዉ እየተገመገመ ፖለቲካዊ ዉሳኔ አየተሠጠ መመራት አለበት ብለዋል ።

በከተማዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በገበያ ማእከላት፣በእሁድና በቅዳሜ ገበያ፣በመጋዘን ክምችት፣ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ያለዉ የግብይት ስርዓት እንዲሁም በአምራች በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ያለዉ የግብይት ሠንሠለት አፈፃፀሙ የተሻለ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ የገበያ ማዐከላትን በመደገፍና በመቆጣጠር እንዲሁም እድሳት በማድረግ ያልገቡትን ወደ ስራ ማስገባት ፣የእሁድና የቅዳሜ ገበያ ቦታዎችን በማስፋፋትና፣በልማት የተያዙ የገበያ ቦታዎች ምትክ በመስጠት ፣አምራች አቅራቢና ሸማችን በማስተሳሰር ፣ተኪ ምርቶችን በማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር መሥራትና በዘይትና በስኳር ላይ ችግሩን ለይቶ አስተማሪ እርምጃ መዉሰድ ይገባል ብለዋል።

የገቢ ምንጭ ከማስፋትና ገቢ ከመሠብሠብ ረገድ በበጀት ዓመቱ የንቅናቄ መድረክ ፈጥሮ በማወያየት የጋራ መግባባት ከመፍጠር፣ፀጋዎቻችንን ከመለየትና ምንጮቻችን ከማስፋት፣እስከ ብሎክ ወርዶ ነጋዴውን ወደ ህግ ስርዓት ከማስገባት ፣በህጋዊ ደረሰኝ ግብይት እንዲፈፀም ከማድረግ እንዲሁም ክትትልና ቁጥጥር ስርዓትን ከማጠናከር የተሰራዉ ስራና በዚህም የእቅዳችንን 84.72 በመቶ በመፈፀም ገቢ መሠብሰብ መቻሉ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አክለዉም ከዚህ በተሻለ ገቢያችንን አሳድገን ትላልቅ የልማት ስራዎቻችንን ለማሳካት በየደረጃዉ ተቋማት አሰራራቸዉን መፈተሽ ችግራቸዉን ማረም ፣መሠረታዊ ንቅናቄ አሰከ ወረዳ ፈጥሮ ግንዛቤ መፍጠር፣ህጋዊ ስርዕት ማስያዝና የተቀራረበ አፈፃፀም እንዲኖር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ሲሉ ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

ግብረ ኃይሉና አመራሩ ከነጋዴዉ ማህበረሰብና ከሌሎች አካላት ጋር በመቀናጀት ያለደረሰኝ የሚነግዱ፣ንግድ ፍቃድ የሌላቸዉ፣ ምርት በመጋዘን የሚደብቁ ፣ዋጋ የሚጨምሩ፣አሳቻ ሠዓት ጠብቀዉ ህገወጥ ግብይት በሚፈፅሙት ላይ የወሰዳቸዉ ህጋዊ እርምጃዎች ህግን ከማስከበር አኳያ የተሻለ ለዉጥ መምጣቱን ገልፀዉ አሁንም ማስተማርን ቀዳሚ ተግባር አድርገን ከዚህ ባለፈ ህግና ስርዓትን የተከተለ ጤናማ የግብይት ስርዓት በዘላቂነት እንዲኖር ህጋዊ እርምጃዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ግብረሀይሉ ስምሪቱን በሽፍት በመጠቀም ቀን ከሌት በትጋትና በቁርጠኝነት ደንብና አሠራርን ጠብቀን መስራት ይጠበቅብናልም ብለዋል።

ለንግዱ ማህበረሰብ እና ለሸማቹ ወቅታዊ የግብይት ስርዓቱን አስመልክቶ በመደበኛና በማህበራዊ ሚዲያ እንዲሁም ህትመት ዉጤቶችን በመጠቀም መረጃን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የንግድ እንቅስቃሴ ወጥ በሆነ መንገድ ለህብረተሰቡ መረጃ የመስጠት እና በዘርፉ ምሁራኖች የሚሳተፉበትና ህብረተሰቡ ሀሳቡን የሚገልፅበት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት የመማማሪያ የዉይይት ፕሮግራም እንዲኖር ማድረግ ለስራችን ስኬት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ ብለዊል ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊና የግብረ ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በበኩላቸው ግብረሀይሉ ከስራ አስፈጻሚ ጋር በቅንጅት መስራቱ ፣ የግንዛቤ መፍጠር ስራ በንቅናቄ መታጀቡ፣ህግ በተቀናጀ አግባብ የማስፈነና አማራጭ የገቢ ምንጮችን በመጠቀምና የገቢ ስርዓትን በማዘመን ገቢን እለት እለት ማሳደግ መቻሉ እና መርካቶ ላይ ወደ ህጋዊ ስርዓት የመግባት ጅምር ዉጤት ያመጣንባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል ።

አክለዉም እነዚህን ተስፋ ሰጪ ጅምር ስራዎች በአደረጃጀትና በአሰራር በማጠናከር ህገ ወጥ ንግድን በሕጋዊ የንግድ ስርዓት መተካትን ጨምሮ በዘላቂነት ገበያ የማረጋጋት ዝርዝር ተግባራትን ግብር -ኃይሉ በዕቅድ እየተከታተለ እንዲፈፅም በማለት ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች በመድረኩ ማብራሪያና ምላሽ መስጠቱና የጋራ ዉሳኔ በሚያስፈልጋቸዉ የበላይ አመራሩ ተወያይቶ አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚሰጥባቸዉ በመግባባት በቀጣይም በተቀመጠዉ የጋራ አቅጣጫ መሠረት ግምገማዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በማጠቃለያ ጥሩ አፈፃፀም ያመጡትን ተቋማት እዉቅና መስጠት እንደሚገባና የአፈፃፀም ዉስንነት ያለባቸዉ ችግራቸዉን ገወምግመዉ በማረም ለቀጣይ የተሻለና የተቀራረበ አፈፃፀም እንዲኖር ማሳሰቢያ መስጠቱን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review