የኢጋድ የህፃናት ጉዳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing የኢጋድ የህፃናት ጉዳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

AMN-ኅዳር 30/2017 ዓ.ም

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የህፃናት ጉዳይ ሚኒስትሮች የህፃናት ፖሊሲ ማዕቀፍን ለማጽደቅ በመጪው ዓርብ በአዲስ አበባ ይሰበሰባሉ።

ስብሰባው የህፃናት ፖሊሲ ማዕቀፍን በማፅደቅ በአባል ሀገራት እና በቀጣናው ያሉ ህፃናት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን ኢጋድ በመግለጫው አስታውቋል።

ይህ ደግሞ አባል ሀገራቱ ለህፃናት መብት መከበር ከገቡት ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ቃል ኪዳኖች ጋር የሚጣጣም ነው ሲል ኢጋድ በመግለጫው ጠቅሷል።

ሚኒስትሮቹ የኢጋድ የህፃናት ፖሊሲ ማዕቀፍን በማጽደቅ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሚኒስትሮች ስብሰባ ከታኅሳስ 4 እስከ 6 ቀን 20217 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከሚኒስትሮቹ ስብስባ አስቀድሞ ታኅሳስ 2 እና 3 ቀን 2017 ዓ.ም የቴክኒክ ባለሙያዎች ስብስባ እንደሚካሄድ ታውቋል።

በስብስባው ላይ የኢጋድ አባል አገራት ሚኒስትሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የልማት አጋሮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለጫው ማመላከቱን ኢዜአአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review