የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በአውርፓ አባል ሀገራት ያሉ የትምህርት ዕድሎችን አስታወቀ

AMN ኅዳር -30/2017 ዓ.ም

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር በአውርፓ አባል ሀገራት ያሉ የትምህርት ፕሮግራም ዕድሎች የማስተዋወቅ ፕሮግራም ተካሂዷል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዓት ማገዝ የሚችሉበትን እንዲሁም ለተማሪዎች አማራጭ የትምህርት ዕድሎችን ማመላከቻ መርሃግብር ነው ያካሄደው፡፡

በመርሃ ግብሩ ከ14 የአውሮፓ አባል ሀገራት የመጡ ተወካዮች የሚሰጧቸውን ነፃና የክፍያ የትምህርት ዕድል ፕሮግራሞቻቸውን ለተማሪዎችና አስተዋውቀዋል ።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም መርሀ ግብሩ የአውርፓ ህብረት የኢትዮጵያ ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና በአውሮፓ የትምህርትና ስልጠና ዕድል ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ለማመለካት የሚያግዝ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በትምህርቱ ዘርፍ ያላቸውን ትብብርም ለማጎልበት ያግዛል ብለዋል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርሃነ መስቀል ጠና ( ዶ/ር ) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከአውሮፓ ህብረት ጋር ግንኙነቱን በማጠናከር ለዜጎች የትምህርት ዕድሉን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

መሰል መርሀ ግብሮች መካሄዳቸው የኢትዮጵያና አውሮፓ ህብረት ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል።

ኤ ኤም ኤን ያጋገራቸው ተማሪዎችም ፕሮግራሙ በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ያሉ የትምህርት ዕድሎች መረጃ እንዲያውቁ እና እንዲገነዘቡ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት በ2016 ለ54 ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቱም በመርሃግብሩ ላይ ተመላክቷል።

በመሀመድ ኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review