
AMN – ታኅሣሥ -2/2017 ዓ.ም
የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በመሰረታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የመንግስት አካላት ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የሲቪክ ማህበራትን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጠየቀ።
ታሕሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ በሚጀምረው የምክክር መድረክ በንቃት ለመሳተፍና ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎች ተለይተው ውይይቱ እንዲሳካ ድርሻቸውን እንዲወጡ ያለመ ውይይት የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የመንግስት አካላት ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የሲቪክ ማህበራትን ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በመሰረታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የመንግስት አካላት ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የሲቪክ ማህበራትን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል ምክክር ቡድን አስተባባሪ አቶ ብዙነህ አስፋ ጠይቀዋል።
ኦሮሚያን ወክለው በምክክር ጉባኤው የሚሳተፉ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ስኬታማ እንዲሆን እና በአጀንዳ ማሳበብ ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑ የማህበረሰብ ተወካዮች የኦሮሞ ሕዝብ እና የሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ብሄር ፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ጥያቄዎችን ማዕከል ያደረገ አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደትን የማመቻቸት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
በዳንኤል መላኩ