
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ “ሀገር ወዳድነት የሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እያካሄደ ይገኛል::
AMN – ታኀሣሥ 3/2017 ዓ.ም
በአራዳ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ኮንፈረንስም የሀይማኖት አባቶች፣የፀጥታ አካላት፣በጎፈቃደኞች፣የሰላም ሰራዊት አባላትና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ፣ መድረኩ ህዝቡ ሰላምን በማፅናት በኩል ሚናውን እንዲወጣ ከማስቻል ባለፈ ወንድማማችነትን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።
ህዝብና መንግስት በቅንጅት መስራታቸው ከተማዋ ሰላማዊ እንድትሆን ብሎም የወንጀል ምጣኔን እንዲቀንስ ያስቻለ ነውም ብለዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ፣ የሰላም ዋጋ የሚለካው ማህበረሰቡ ለሰላም ያለው ዕይታና አመለካከት እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ተሳትፎ ሲታከልበት ነው ብለዋል።
በትዕግስት መንግስቱ

All reactions:
4848