
AMN – ታኅሣሥ -5/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀን ከፍተናልም ብለዋል።
ማዕከሉ ወላጅ የሌላቸውንና በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ያመለከቱት።