የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) በድሬዳዋ የኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው

You are currently viewing የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) በድሬዳዋ የኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው

AMN- ታኅሣሥ 7/2017 ዓ.ም

የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) በድሬዳዋ አስተዳደር የኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኙ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ ባለፉት ሶስት ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ገጠር እና ከተማ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።

ዛሬ ደግሞ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተደረገ ድጋፍ ወደ ማምረት የተሸጋገሩ ኢንዱስትሪዎችን የልማት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው።

በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ መንደር የመካከለኛና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያመርቱትን የጨርቃጨርቅና የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን ተመልክተዋል።

በተጨማሪም በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን እና የደረቅ ወደብ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተው አበረታትተዋል።

ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ላይ የሚገኘውን ሃሴት የመድኃኒት ቁሶች ማምረቻ ፋብሪካንም እንዲሁ።

በጉብኝቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ እና የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራር አባላት ተሳትፈዋል።

ሚኒስትሩ የድሬዳዋ ካይዘን ኢንስቲትዩት ተቋምን እየገበኙ ሲሆን፤ በማዕድን ዘርፍ የተከናወኑትን ጨምሮ ሌሎች የልማት እንቅስቃሴዎችን ይመለከታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review