የተሰረቀ ንብረት በሚገዙ ህገ ወጦች ላይ በተደረገ ክትትል ልዩ ልዩ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮች ተያዙ

You are currently viewing የተሰረቀ ንብረት በሚገዙ ህገ ወጦች ላይ በተደረገ ክትትል ልዩ ልዩ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮች ተያዙ

AMN – ታኀሣሥ 7/2017 ዓ.ም

የተሰረቀ ንብረት በሚገዙ ህገ ወጦች ላይ ባደረገው ክትትል ልዩ ልዩ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮች መያዙን የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የተሰረቀ እቃዎችን በተለይም የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን በሚገዙ ህገ-ወጦች ላይ በተደረገ ክትትል በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ ከ60 በላይ ሞባይል ስልኮችና ታብሌቶች ተይዘው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲቲ ሞል እና ወረዳ 2 ቅዱስ ዮሃንስ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ የሚገኙ ሁለት ንግድ ቤቶች ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቁ ንብረቶችን ከሌቦች እንደሚገዙ ፖሊስ ያሰባሰበው ማስረጃን ተከትሎ በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ በልዩ ልዩ ጊዜያት የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችና ታብሌቶች መያዛቸው ታውቋል፡፡

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የተሰረቀ እቃ በመግዛት የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ገልፆ ንብረታቸው የጠፋባቸው አራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ መረከብ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ በወንጀሉን አፈፃፀም ተጠርጣሪ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቆ ህጋዊነት ከህገ-ወጥነት ጋር እየቀላቀሉ የሚሰሩ ግለሰቦች ከህገ-ወጥ ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ ፖሊስ የተሰረቁ እቃዎችን በሚገዙ ግለሰቦች ላይ እያደረገ ያለውን ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review