AMN-ታህሣሥ 16/2017 ዓ.ም
ብልጽግና ፓርቲ ካለፉት ስርዓቶች በተሻለ ለከተሞች ሁለንተናዊ እድገት ትኩረት የሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆው የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡
ፓርቲው ባለፉት አመታት ከሌሎቹ ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ ለከተሞች ሁለንተናዊ ልማት ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ለከተሞች በተሰጠው ትኩረት ውስጥ የኢትዮጵያ ምልክት እና መታያ የሆነችው አዲስ አበባ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቷን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ባለፉት አመታት በከተማዋ የተሰራው ስራ ውጫዊ ገጽታዋን ከማሳመር በላይ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወነው የልማት ስራ በዋነኛነት የነዋሪውን ህይወት ማሻሻል ላይ ማተኮሩን የገለጹት ከንቲባዋ ይህም ከፓርቲው ሰው ተኮር ፖሊሲ የመነጨ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጡን ከሚጠበቀው አንጻር የበለጠ ማሻሻል ፣ የመኖሪያ ቤት ችግርን እና መሰል የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን መፍታት የፓርቲው የቀጣይ የከተሞች ልማት ትኩረት እንደሚሆንም ነው ከንቲባ አዳነች ያስታወቁት፡፡
አዲስ አበባ ከተማን መነሻ አድርጎ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች የተስፋፋው የኮሪደር ልማት መርሃ ግብርም የህዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሆኑን ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡
የኮሪደር ልማት ስራው በከተሞች መካከል በጎ የፉክክር መንፈስን የፈጠረ፣ በመንግስት ልዩ ትኩረት እና ክትትል የሚገነባ እና ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በሰብስቤ ባዩ

All reactions:
140You, Tekalign A Buki, Tsehhay Habte and 137 others