AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም
ይህ አዲስ አገልግሎት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ስራ ላይ ለተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ኢስላሚክ መርህን ማዕከል ያደረገ በተለይም ለሴቶች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ ትልቅ እምርታ ነው ተብሏል፡፡
የዲጂታል አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
ባንኩ ከዲጂታል ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ሙሉ በሙሉ ሸሪዓን መሰረት ያደረገ የዲጂታል ፋይናንስ መተግበሪያ አንሳር ዲጂታል ፋይናንሲንግ በይፋ ማስጀመሩን የገለፁት የዘምዘም ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ መሊካ በድሪ ናቸው፡፡
አንሳር የዲጂታል አገልግሎት ስርዓት የባንኩን ተደራሽነት ከማስፋት በላይ በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ ላለው ማህበረሰብ የፋይናንስ እጥረትን ለመቅረፍ አይነተኛ መፍትሄ ነውም ብለዋል።
ዘምዘም ባንክ ሸሪዓን መሰረት ያደረገ ዲጂታል ፋይናንስ መተግበሪያን በማስጀመር ፈር ቀዳጅ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ናቸው።
በባንኩ ይፋ የተደረገው መተግበሪያ እንደ ሀገር ያለውን ፋይናንሽያል ሲስተም የሚያጠናክር እንዲሆን ያደርጋል ያሉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሩ ሁሪያ አሊ ባንኩ ባስቆጠረው አጭር የአገልግሎት ጊዜ አርዓያ የሚሆን ስራ ስለመስራቱ አንስተዋል።
በጽዮን ማሞ