ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ100 ሺህ ዶላር ቦንድ ለመግዛት አቅደናል:- የዱባይና ሰሜን ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር

You are currently viewing ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ100 ሺህ ዶላር ቦንድ ለመግዛት አቅደናል:- የዱባይና ሰሜን ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር

AMN- መስከረም 22/2017 ዓ.ም

የዱባይና ሰሜን ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር በተያዘው ዓመት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የ100 ሺህ ዶላር ቦንድ ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ።

የግድቡ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አሁንም ቢሆን የዳያስፖራውም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ወገኖች ድጋፋቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የዱባይና ሰሜን ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር፤ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጧል።

የማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ኢድሪስ ቡንሱር፤ በኢትዮጵያ የልማት፣ የኢንቨስትመንትና የሰብአዊ ድጋፍ ሥራዎች ላይ ማኅበሩ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ ይህንንም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት እስካሁን የ550 ሺህ ዶላር የቦንድ ግዥ መፈፀሙን አስታውሰው፤ አሁንም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም በ2017 ዓ.ም ለግድቡ ግንባታ የ100 ሺህ ዶላር የቦንድ ግዥ ለማከናወን ማኅበሩ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

በማኅበሩ ለገበታ ለሀገር፣ ለጽዱ ኢትዮጵያና ሌሎችም ኢኒሼቲቮች የ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ድርሃም ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ለመሰል የልማት ሥራዎች እገዛው ይቀጥላል ሲሉ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዱባይና ሰሜን ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበር ከተመሠረተ 25 ዓመታትን ማስቆጠሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review