AMN – ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች በድጋሚ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል 5 ሺህ የሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ተበረከተ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ በንፅህና መጠበቂያ ምርት ላይ በሚስተዋለው የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም፣ የዋጋ ውድነትና ጥራት መጓደል ምክንያት ሴቶችና ልጃገረዶች ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
ይህ ችግር በይበልጥ ጎልቶ የሚታየው በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና ዩኒቨርስቲዎች ላይ መሆኑን በመገንዘብ ሚኒስቴሩ ከቱርክ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንዳበረከተ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝንዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ለሴት ተማሪዎች የተበረከተው ስጦታ የወደፊቷ ባለ ብሩህ አዕምሮ የኢትዮጵያ ሴት ልጆች ለማፍራትና ችግሮችቻቸውን በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የቱርክ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ኃላፊ ኤንቨር ረሱልጉላሪ ኤጀንሲው በኢትዮጵያ በጤና፣ በትምህርት፣ ሰብዓዊ ድጋፎችን ጨምሮ በተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተሳተፈ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።